Posted by: mmeazaw | January 25, 2011

የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር ከኢሕአዴግ አመራርነት ወደዕጩ አባልነት ዝቅ ተደረጉ


‹‹ካልተሳሳትኩ ግለሰቦች የፈጠሩት የሥልጣን ሽኩቻ ይመስለኛል›› አቶ አዲሱ መንግሥቱ

በታምሩ ጽጌ
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የኢህአዴግ አባላት ሰሞኑን ባደረጉት የአንድ ቀን ግምገማ፣ ምክትል ኮሚሽነር አዲሱ መንግሥቱን ከከፍተኛ አመራርነት ወደዕጩ አባልነት ዝቅ አደረጓቸው፡፡

አንዳንድ ሰዎች በእሳቸው ላይ ደስተኛ ስላልሆኑ መልካም ስማቸውን ለማጉደፍ ያደረጉት መሆኑን አቶ አዲሱ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ አዲሱ ወደዕጩ አባልነት ዝቅ እንዲሉ የተደረጉበት ምክንያት ከአንድ ዓመት በፊት በኮሚሽኑ በጀት ባለ10 ሺሕ ብር የሞባይል ቀፎ ካስገዙ በኋላ፣ ለቀናት ከተጠቀሙበት በኋላ ‹‹መልኩ ደስ አይልም›› ብለው በተመሳሳይ ወጪ ሌላ ሞባይል አስገዝተዋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ባለ18 ሺሕ ብር አይፎን ሞባይል በማስገዛት የመንግሥትን ሀብትና ንብረት ላልተፈለገ ዓላማ አውለዋል በሚል ነው፡፡

ከሁለት ዓመታት በላይ የድርጅት ክፍያ ስላልከፈሉ ከአባልነት መባረር እንዳለባቸው፣ ከሁለት ዓመት በፊት የእንግዳ መቀበያ ሶፋ በ30 ሺሕ ብር ከማስገዛታቸውም በተጨማሪ፣ በቅርቡ የ35 ሺሕ ብር ሶፋ በድጋሚ ማዘዛቸውን በማንሳት መገምገማቸው ተወስቷል፡፡

አቶ አዲሱ ሁለት የመንግሥት ቤት በመያዝ ባንዱ እየኖሩ አንዱን እያከራዩ መሆናቸውን፣ የኮሚሽኑን ደንብ በጣሰ አሠራር 5000 ብር ለግላቸው መጠቀማቸውን፣ ለድርጅቱም ሆነ ለመንግሥት ሥራ ደንታ እንደሌላቸው በመግለጽ መገምገማቸው ተገልጾ፣ በድርጅቱ (ኢሕአዴግ) ስብሰባ ላይ ላለመገኘት የተለያዩ ምክንያቶችን እንደሚፈጥሩ፣ ለግምገማ ሲፈለጉ እንደሚሸሹ፣ የሚጨነቁት ለሥራቸው ሳይሆን ለክብራቸው መሆኑንና ሌሎች በርካታ ነጥቦችን በማንሳት መገምገማቸውን ተናግረዋል፡፡
በኮሚሽኑ የኢሕአዴግ አባላት በመጨረሻ አቶ አዲሱ ከአመራርነት ወደዕጩ አባልነት እንዲወርዱ፣ በትርፍ የያዙትን የመንግሥት ቤት ባስቸኳይ እንዲመልሱ፣  በትርፍ የያዙዋቸው ሞባይሎችን እንዲመልሱና የሦስት ዓመታት የድርጅት የአባልነት ክፍያ ከፍለው እንዲያጠናቅቁ በሙሉ ድምፅ መወሰናቸው ታውቋል፡፡

የድርጅቱ አባላት የወሰዱትን ዕርምጃ በሚመለከት ማብራሪያ እንዲሰጡን ያነጋገርናቸው ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዲሱ መንግሥቱ እንደገለጹት፣ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አንዳንድ አባላት በእርሳቸው ደስተኞች ስላልሆኑ መልካም ስማቸውን ለማጉደፍ ያደረጉት ነው፡፡

በግምገማው ወቅት መሳተፋቸውንና የተባለውን ሁሉ አንዱንም እንዳልተቀበሉትና ከእውነት የራቀ መሆኑን የገለጹት አቶ አዲሱ፣ የድርጅቱን አባላት የሰበሰባቸው አንድ ሰው መሆኑንና አለቃቸው በመሆኑ በመፍራት ያስተላለፉት ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በድርጅቱ አባልነት ለ17 ዓመታት መቆየታቸውን፣ ለኮሚሽኑም ከኤክስፐርትነት እስከምክትል ኮሚሽነርነት ሲሠሩ በቆዩባቸው ዓመታት ማንነታቸው በመላው ኢትዮጵያ ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ትላልቅ የትምህርት ተቋማትና በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ሳይቀር የሚታወቁት በንፅህናቸው መሆኑን አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

‹‹ለጊዜው ለስሜም ሆነ ከሥራዬ አኳያ ከእነሱ ጋር ንትርክ ውስጥ መግባት ስላልፈለግኩ ለመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች አሳውቄያሁ፤›› ያሉት አቶ አዲሱ፣ ለስድስት ዓመታት በኮሚሽኑ ውስጥ ሲሠሩ አንድም ቀን ምንም ዓይነት ነገር ሳይነሳባቸው አሁን እንደዚህ ያለ ነገር መደረጉ እንዳሳዘናቸውና እንዳስገረማቸው ተናግረዋል፡፡
ማንኛውንም ነገር በሰፊው ወደ ፊት እንደሚገልጹና እውነቱንም እግዚአብሔር እንደሚያወጣው የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ ‹‹ካልተሳሳትኩ ግለሰቦች የሚያደርጉት የሥልጣን ሽኩቻ ይመስለኛል፤›› ብለዋል፡፡

ሪፖርተር

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Categories