Posted by: mmeazaw | July 5, 2010

ፋሲለደስ


ፋሲለደስ

አፄ ፋሲለደስ (የዙፋን ስማቸው ዓለምሰገድ) ከአባታቸው አፄ  ሱሰኒዮስእና እናታቸው ልዕልት ስልጣነ ምገሴ በመገዛዝሸዋ ህዳር 10 1603 (..) ተወለዱ። የነገሱበትም ዘመን 1632 እስከ ጥቅምት 18, 1667 (..) ነበር።

ንግስና

ስረፀ ክርስቶስ በተመራው አመፅ ምክንያት በ1630 ፋሲለደስ ለንግስና ቢበቃም፣ ዘውዱን ግን እስከ 1632 አልጫነም ነበር። ሲመተ ንግስናው በ1632 እንደተገባደደ የመጀመሪያው ስራው የተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንን የቀድሞው ቁመና መመለስና የካቶሊኮችን መሬት በመቀማት ከደንካዝ በማባረር በፍሪሞና እንዲወሰኑ ማድረግ ነበር። ወዲያውም በማከታተል ከግብፅ አገር አዲስ ጳጳስ እንዲላክለት በማድረግ በአባቱ ዘመን እንዲደበዝዝ ተደርጎ የነበረውን የግብፅና ኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት እንዲጸና አደረገ። በኬኒያ የሚገኘው የሞምባሳ ወደብ በፖርቱጋሎች መደብደቡን ሲሰማ፣ የሮማው ፓፓ ከበስትጀርባው ያለበት ሴራ ነው በማለት በምድሩ የነበሩትን የካቶሊክ ጀስዊቶች በመሰብሰብ አባረራቸው።
ጎንደር ከተማ
ፋሲለደስ የጎንደር ከተማን በ1636 የኢትዮጵያም ዋና ከተማ እንደቆረቆራት ይታመናል። ከሱ በፊት በአካባቢው ከተማ እንደነበር ወይም እንዳልነበር በታሪክ የተገኘ ማስርጃ እስካሁን የለም። አከታትሎም የፋሲል ግቢን44ቱ ታቦታት ተብለው የሚታወቁትን የጎንደር ከተማ አብያተ ክርስቲያናት መሰረት ጣለ። በአፄ ፋሲል ከተመሰረቱት ታዋቂወቹ 44 አብያተ ክርስቲያናት፣ ታዋቂወቹ አደባባይ እየሱስአደባባይ ተክለ ሃይማኖትአጣጣሚ ሚካኤልግምጃቤት ማራያምፊት ሚካኤል፣ እና ፊት አቦ ይገኙበታል። [2] ያለመታከትም 7 የድንጋይ ድልድዮችን በማሰራት እስካሁን ድረስ ስሙ ሲጠራ ይኖራል። አልፎም በግርኝ አህመድ ዘመን በእሳት ጋይቶ የነበረችውን አክሱም ፂዮን በአዲስ መሰረት እንደገና ማሰራት ችሎአል። ፋሲለደስ በዘመኑ እጅግ ተወዳጅ ንጉስ ቢሆንም አመጽ መነሳቱ አልቀረም። በላስታ ለምሳሌ በ1637 መልክዓ ክርስቶስ በተባለ ሰው መሪነት ጦርነት ተነስቶ አፄ ፋሲልን ስጋት ላይ ቢጥልም በሚቀጥለው አመት በተደረገው ጦርነት አመፁ ሊገታ ችሎአል። ፋሲለደስ ፖርቱጋሎችን ቢያባርርም ከውጭው አለም ጋር ብዙ ግንኙነት ያደርግ ነበር። ለምሳሌ በ1664-5 የህንድ ንጉስ አውራንግዘብ ሲነግስ መልካም ምኞትን በመልክተኞቹ ለሙግሃሉ መሪ ልኮ ነበር። በ1666 ልጁ ዳዊት ሲያምጽ፣ ወህኒ ተብሎ ወደሚታወቀው አገር በግዞት ልኮት ነበር። ይህም ከጥንቶቹ የኢትዮጵያውን ነገሥት ተፎካካሪያቸውን ወደ አምባ ግሽን በግዞት እንደሚልኩት ስርዓት ነበር።

የፋሲል እረፍት
አፄ ፋሲል አዘዞ ተብላ በምትታወቀው ከጎንደር ከተማ 5 ማይል ርቃ በምትገኘው ከተማ ጥቅምት18፣1667 ከዚህ አለም በሞተ ተለዩ። አስከሬናቸውም የአገሪቱ መላ ህዝብ ባዘነበት ሁኔታ በቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም፣ ጣና ሃይቅ ውስጥ ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው ደሴት የዘላለም እረፍት አገኘ። መቃብራቸውም ውስጥ ያንድ ትንሽ ህፃን አስክሬን አብሮ ይገኛል። ይሄውም ልጃቸው ሲሆን የወደፊቱ ንጉስ ለመሆን እጩ ነበር። ነገር ግን አዲሱን ንጉስ የመጣው ህዝብ ብዛት ሲተራመስ ድንገት ተጠቅጥቆ ለሞት በቃ።.

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Categories